"እግዚአብሔር በአንድም መንገድ በሌላም ይናገራል።" ኢዮ.33፥14

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ይህ ሶፍትዌር ከዚህ በፊት 2000 .. /..አ. በ2008 / በተለቀቀው ሶፍትዌር ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች በማድረግ ማተም /ፕሪንት ማድረግ/ ንዲቻል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። ወደ ኮምፒዩተርዎ በመጫን ይጠቅሙ።

BahireHasabSetupIcon.JPG ሶፍትዌሩን እዚህ በመጫን ይጠቅሙ።

001mksebketwongel1

ለመቀሌ ዓይነ ዓለም ደብረ ኃይል ቅዱስ ጊዮርጊስ ኣንድነት ገዳም ማኅበረ መነኮሳት የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ

ሰኔ 22 ቀን 2007 ዓ.ም.

ዲ/ን ኃይለ ሚካኤል ኃይሉ/ከመቀሌ ማእከል/

001mekeleበማኅበረ ቅዱሳን የመቀሌ ማእከል በመቀሌ ሀገረ ስብከት ውስጥ ለሚገኘው ዓይነ ዓለም ደብረ ኃይል ቅዱስ ጊዮርጊስ ኣንድነት ገዳም ከ30 በላይ ለሚሆኑ አረጋውያን መነኮሳትና መነኮሳይያት ከ7500 በላይ ወጪ በማድረግ የብርድ ልብስ ድጋፍ አደረገ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርትን አስመረቀ

ሰኔ 20 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

001temerakiየቅድሰት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በሁለተኛ ዲግሪ፤ በቀንና በማታ በመጀመሪያ ዲግሪ ፤ በዲፕሎማ፤ እንዲሁም በርቀት ትምህርት 303 ደቀመዛሙርትን ሰኔ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ አስመረቀ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
መምህረ አንጢላርዮስ ምጽዋት


መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

ሰኔ 20 ቀን 2007ዓ.ም

አንጢላርዮስ የሚባል ለተቸገረ የማያዝን፣ ለተራበ የማይራራና የማይሰጥ ንፉግ ባለጸጋ ሰው ነበር፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን ነዳያን በመንገድ ተቀምጠው ሳለ አንጢላርዮስ ሲያልፍ አይተው ይህ ጽኑ ጨካኝ ባለጸጋ፤ ለተቸገረ ሰው የማያዝን ተባባሉ፡፡ ከመካከላቸውም አንዱ ግን ሄጄ ሰጥቶኝ በልቼ ጠጥቼ ብመጣስ አላቸው፡፡ እነርሱም አብልቶ አጠጥቶህ አትመጣም፡፡ እንዲያውም አይሠጥህም ሲሉ መለሱለት፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
የአብነት ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ዲቁና ተቀበሉ

ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓ.ም.

ከደብረ ብርሃን ማእከል

001diakonatበማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ብርሃን ማእከል አማካኝነት የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 25 የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ እና የመምህራን ኮሌጅ ግቢ ተማሪዎች ሰኔ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ከብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዲቁና ተቀበሉ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
የመላእክት እንጀራ ይበላል በቅድስና

ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓ.ም.

ክፍል አንድ

ከማኅበረ ቅዱሳን መዝሙርና ሥነጥበባት ክፍል

በዚህ ዓምድ መዝሙሮቻችን ወዴት እየሔዱ እንደሆነ ያሳሰበው የማኅበረ ቅዱሳን መዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል ያዘጋጀልንን ጽሑፍ አቅርበናል፡፡ መዝሙር ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚነጋገሩበት ምስጋናቸውን የሚገልጡበት፣ ከኀዘናቸው የሚጽናኑበት፣ የእግዚአብሔር ማመስገኛ የጸሎት ክፍል ነው፡፡ የጸሎት ክፍል በመሆኑም ምድራውያን ከሰማያውያን፣ ሰማያውያን ከምድራውያን ጋር አንድ የሚሆኑበት፣ የዚህን ዓለም ፃዕር ጋዕር ረስተው ወደ ሌላ ዓለም በመንፈስ የሚመሰጡበትና የሚነጠቁበት ከፈጣሪ ለሰው ልጅ የተሰጠ ጸጋ ነው፡፡ የመዝሙርን ትርጉም ሊቃውንት እንዲህ በይነውታል፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
ዝርዝር ፅሁፍ...
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 1 ከ 48