"እግዚአብሔር በአንድም መንገድ በሌላም ይናገራል።" ኢዮ.33፥14

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ይህ ሶፍትዌር ከዚህ በፊት 2000 .. /..አ. በ2008 / በተለቀቀው ሶፍትዌር ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች በማድረግ ማተም /ፕሪንት ማድረግ/ ንዲቻል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። ወደ ኮምፒዩተርዎ በመጫን ይጠቅሙ።

BahireHasabSetupIcon.JPG ሶፍትዌሩን እዚህ በመጫን ይጠቅሙ።

የዐቢይ ጾም ሳምንታት
የትንሣኤው ትርጉምና የሰሙነ ፋሲካ ዕለታት አትም ኢሜይል

ሚያዝያ 24 ቀን 2008ዓ.ም.

ትንሣኤ የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም ተንሥአ = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡ ትንሣኤ ማለት = መነሣት፣ አነሣሥ፤ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡ ትንሣኤ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም አምስት ክፍሎች አሉት፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ የፋሲካን በዓል ታከብራለች፡፡ /ድጓ ዘፋሲካ/ አትም ኢሜይል

ሚያዚያ 22ቀን 2008ዓ.ም

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

በጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ አሳሳችነትና ምክር አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ሕግ ተላልፈው ሞተ ሥጋና ሞተ ነፍስ ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምና ሔዋን ከክህደት፣ ከስህተት የደረሱት በዲያቢሎስ አሳሳችነት በመሆኑ እንዲሁም ለሰው ልጆች ካለው ፍጹም ፍቅር የተነሳ የተፈረደባቸውን ሞት በሞቱ ሊደመስስ ሰው ሆነ፡፡ ዮሐ1፡1 ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ 30 ዓመት ሲሞላው ተጠመቀ፡፡ እንደተጠመቀም ልዋል ልደር ሳይል ገዳመ ቆሮንቶስ ሄደ፡፡ በዚያም ጾመ ጸለየ በዲያቢሎስም ተፈተነ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
ጌታችን በመስቀል ላይ የተናገራቸው ሰባቱ አጽርሐ መስቀል አትም ኢሜይል

ሚያዝያ 21 ቀን 2008 ዓ.ም

1.ኤሎሄ አሎሄ ላማ ሰበቅታኒ፡-

005sikletአምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ማለት ነው፡፡ ማቴ.26፡47፡፡ ይህን አሰምቶ የተናገረው በዘጠኝ ሰዓት ነው፡፡ እርሱ አምላክ ሆኖ ሳለ አምላኬ አምላኬ ብሎ የተናገረው ለምንድነው ቢሉ ከሕገ እግዚአብሔር ርቆ ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን የተተወ የአዳምን ሥጋ ተዋሕዶ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጥ ነው፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
ሥርዓተ ሰሙነ ሕማማት፡- ዕለተ ዓርብ አትም ኢሜይል

ሚያዝያ 20 ቀን 2008 ዓ.ም

ዕለተ ዓርብ ነግህ

ዕለተ ዓርብ የአዳምን ነጻነት ለመመለስ የአዳምን ዕዳ በደል አምላካችን የተሸከመበት ዕለት፣ የኃዘን ዕለት፣ የድኅነትም ዕለት ነው፡፡ በዚሁ ዕለት ሁሉም ነገር እንደተለመደው ይከናወናል፡፡ መሪው እዝል ይመራል፣ ሕዝቡ ይከተላል፣ ዐራቱ ወንጌላት ይነበባሉ፡፡ በየመሐሉ ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት፣ ሲነጋም ሊቃነ ካህናት ተማከሩ የሚለው ዜማ በመሪ በተመሪ፣ በሕዝብ ተሰጥዎ ይከናወናል፡፡ ምንባቡም ስግደቱም ድጓውም እንደ አለፈው ይቀጥላል፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
ሰሙነ ሕማማት /ዘረቡዕ/ አትም ኢሜይል

ሚያዝያ 19 ቀን 2008 ዓ.ም

ረቡዕ፡- ምክረ አይሁድ ይባላል፡፡ ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱን የሚያደንቁ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 1 ከ 14